ስለ አካዳሚው
የአካዳሚው አጭር ገጽታ
የአመራር አካዳሚው ቀደም ሲል የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሥራ አመራር ተቋም በክልሉ መንግሥት በአዋጅ ቁጥር 15/1989 የጥናት፣ ምክርና ስልጠና አገልግሎቶችን እንዲሰጥ የተቋቋመ ቢሆንም የተሰጠውን ተልዕኮ በሚፈለገው ሁኔታ መወጣት ባለመቻሉ የክልሉ መንግስት በደንብ ቁጥር 155/2006 በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላትንና ሰራተኞችን የክልሉን የልማት፣ የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግቦች በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም እንዲቻል ለአመራሮችና ባለሙያዎች የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ስልጠና፣ የምክርና፣ የጥናትና ምርምር አገልግሎቶችን እንዲሰጥ በአዲስ መልክ የደቡብ መለስ አመራር አካዳሚ ተብሎ የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 178/2011 የአካዳሚው ስያሜ ደቡብ አመራር አካዳሚ በሚል የስያሜ ማስተካከያ ተደርጎ መልሶ የተደራጀ ተቋም ነው፡፡
በመሆኑም አካዳሚው እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ለ 42,777 በተለያዩ ደረጃ ላሉ ፈጻሚዎችና አመራሮች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በ 66 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማካሄድ ሚናውን ሲወጣ ቆይቷል፡፡ ከ2016 ዓም ጀምሮ በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መልክ ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ ደግሞ ለ2315አመራሮችና ፈጻሚዎች በልዩ ስልጠና፣ በሊደርሺፕ ስልጠናችና በሥራ አመራር ስልጠና ዘርፎች ያሰለጠነ ሲሆን በቁጥራቸው በ 7 የተለያዩ የጥናትና ምርርም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን የክልሉን አፈጻጸም ችግሮች በመፍታት የድርሻውን ተወጥቷል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ በአዋጅ 29/2016 መሰረት በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ ተልዕኮ ተሰጥቶት በሳጃ ክላስተር ከተቋቋመ በኋላ የአሰራር ሥርዓቶች /ሌጅስሌሽን፣ የስልጠናና የጥናትና ምርምር ፖሊሲዎች፣ የአካዳሚው የአደረጃጀት መዋቅርና የጥቅማጥቅም መመሪያዎችን/ ለማጸደቅ የማስተካከያ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡