የአካዳሚው ሥልጣንና ተግባር
የአካዳሚው ሥልጣንና ተግባር
አካዳሚው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 29/2016 መሰረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
- ደረጃውን የጠበቀ የአመራር ልማትና ሥራ አመራር ልማት ሥልጠና፣ ጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎትፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፤ማኑዋሎች፣ ካሪኩለሞች እና ሌሎችንም ስርዓቶችይቀርጻል፤ ይተገብራል፤
- የክልሉን የአመራርና ፈፃሚ ኃይሎችን የስልጠና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ በአመራር ልማት እና በሥራ አመራር ልማት ዙሪያ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ለሚሰጠዉ ስልጠና የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- በክልሉ አዳዲስና ተተኪ ወጣትና ሴት መሪዎችን በማሰልጠን እና በማማከር ብቁ አመራር የማፍራት ሥራ ያከናውል፤
- ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል፣ ሥልጠናውንም ይሰጣል፤
- የሰልጣኞች መመልመያ መስፈርት ያዘጋጃል፣ በመስፈርቱ መሠረትም ይቀበላል፣ የዕለት ተዕለት ግንባታቸው ይከታተላል፤እንደአስፈላጊነቱም ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
- በመንግስት ፖሊሲዎችና አስተዳደር፣ በፖለቲካ ስርአት ግንባታ ዙሪያ፣ ለአመራሩ ውጤታማነትና እድገት ጠቃሚ የሆኑ፣ የክልሉን መንግስትን፤ ተቋማትን፣ እና የአመራሩን ፍላጎትና ክፍተቶችማዕከል ያደረጉ ጥናትና ምርምሮች ያካሂዳል፤ ለክልሉ መንግሥት ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣
- የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ያሳትማል፣ ጆርናሎችን በማዘጋጀት በተለያዩ መንገዶች ያሰራጫል፤ ያሰርጻል፤
- የስልጠና ውጤታማነት ጥናት ያካሂዳል፣ ለሚመለከተው አካልም ሪፖርት ያቀርባል፣ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት የተሻሉ የአሰራር ስልቶችን ይቀይሳል፤
- በወቅታዊ በዓለም-ዓቀፋዊ፤ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች እንዲሁም በተጽዕኖቻቸው ዙሪያ በጥናት ላይ የተደገፈ ትንተና ያካሄዳል፤ ውጤቱንም ለፖሊሲ አውጪዎች ያቀርባል፣
- ለመንግስት መሥሪያ ቤቶች ወይም ተቋማት ወይምለሲቪክ ማህበራት ወይም ለግል ድርጅቶች በጥናትና ምርምር ምልከታና ትንተና ላይ ተመስርቶ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
- በመንግስት ፖሊሲዎችና አስተዳደር፣ በአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ በፖለቲካ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው የክልሉ እና የሀገር ውስጥ አቻና ተባባሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ሴሚናሮችና፣ ሲምፖዚየሞችን፤ ዎርክሾፖችን፤ ኮንፈረንሶችን ያዘጋጃል፣
- የአስፈጻሚና የፈጻሚዎችን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት የሚያሳድጉ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር የሚረዱ የተመረጡ ልምዶችን በመቀመር የዕውቀትና የልምድ ሽግግር ያካሂዳል፤
- የአመራር ደረጃዎች፣ የብቃት መለኪያዎች እና የምዘና ሥርዓት ሀሳብ ያመነጫል፣ ለክልሉ መንግሥት ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣
- የአካዳሚውን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል ተቋማዊ የሰው ሀብት ልማት ስትራቴጂ ይቀርፃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በተፈቀደለት መዋቅር ሥራ መደቦች ላይ ለአካዳሚው የሚያስፈልጉ ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ያሰናብታል፤
- የሥልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና የማማከር ሥራን በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ይሰጣል፣ ሀገር አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ያሳድጋል፤
- በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ውስጥ ከሚገኙ ተመሳሳይ ተልዕኮና ዓላማ ካላቸው ተቋማት ጋር በሥልጠና፣ በጥናትና ምርምር እና በማማከር መስክ የትብብር ግንኙነት ይመሰርታል፤
- በአካዳሚው የሚሰጠው የአመራርና የፈጻሚዎች ሥልጠናና የማማከር አገልግሎት መሠረት አድርገው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ አመራሮችንና ፈጻሚዎችን በማወዳደር ሽልማትና ዕውቅና ይሰጣል፣ ዝርዝሩ አካዳሚው በሚያወጣው የውስጥ መመሪያ ይወሰናል፤
- የሥልጠና፣ የጥናትና ምርምር ክፍሎችን ያቋቁማል፣ ቤተመጽሕፍት ያደራጃል፤
- አካዳሚው ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች እንደአስፈላጊነቱ ተገቢውን የአገልግሎት ሽያጭና ግዢ ክፍያ ይፈጽማል፤ ይሰበስባል፣ የውስጥ ገቢ ያመነጫል፣ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ይቀይሳል፣ አካዳሚው በሚያወጣው የውስጥ መመሪያ መሠረት በቦርድ አስወስኖ ጥቅም ላይ ያውላል፤
- በሥራ አመራር ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ የግል አማካሪዎች የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ሰርቲፊኬት ይሰጣል፣ አቅማቸውን ይገነባል፤አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤በየዓመቱ ያድሳል፤ እንደአስፈላጊነቱ ህጋዊ እርምጃዎችንም ይወስዳል፡፡ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል፡፡
- የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በአካዳሚዉ ስም ይከሳል ይከሰሳል፣
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
ስለአመራር አካዳሚው መቋቋም፤ሥልጣን እና አደረጃጀት
መቋቋም እና ተጠሪነት
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የአመራር አካዳሚ (ከዚህ በኋላ በአጭሩ “አካዳሚው” እየተባለ የሚጠራ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የአመራር አካዳሚ ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፤
አካዳሚው በሕግና በሙያው የሚኖረው የአስተዳደርና የአካዳሚ ነጻነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ተጠሪነቱ ለክልሉ መንግስት ርዕሰ-መስተዳድር እና ለአካዳሚው ቦርድ ይሆናል፡፡
የአካዳሚዉ የሥራ ቦታ/ ዋና መስሪያ ቤት
የአካዳሚው ዋና መስሪያ ቤት ሳጃ ከተማ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ አስተዳደር እርከኖች ቅርንጫፎች ሊኖሩት ይችላል፡፡