ተልዕኮ ራዕይና እሴት
ዓላማ
ዝርዝር ዓላማዎች
- ዕውቀትንና እውነትን የተላበሱ፣ ለህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ፣ በሥራቸውና በምግባራቸው ብቁ አመራሮችንና ፈጻሚዎችን በየደረጃው በብዛት በመገንባት የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና በዘላቂነት ማረጋገጥ፤
- በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ፣ በንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር፣ ሁሉን አቀፍ እና ተደራሽ የአመራርና የፈጻሚዎች ሥልጠና ሥርዓት መዘርጋትና ማጠናከር፤
- ወቅታዊ ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚነሱ ሀሳቦች ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የተለያዩ መድረኮችንና ፎረሞችን በማዘጋጀትና በማማከር የአመራር እና ሥራ አመራር ልማትን ማሳደግ፤
- የአመራር ልማትና የሥራ አመራር ልማት ሥልጠና፣ጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ለተሳካ ክልላዊ ተቋማዊ ግንባታ እውን መሆን ኃላፊነቱን መወጣት የሚችል አመራርና ፈጻሚዎችን በማፍራትለሀገራዊ የብሔረ-መንግስትናሀገረ-መንግስት ግንባታ አስተዋጾኦ ማድረግ፤
- የሀገሪቱን የአመራር ልማት ፖሊሲ ማዕቀፉን መሠረት ያደረገ የአመራር ልማት ሥልጠና በማካሄድየመንግስት ፖሊሲ ሪፎርም አጀንዳዎች በውጤታማነት መፈጸምና ማስፈጸም የሚችል ብቃት ያለው አመራርና ፈጻሚዎችን ለመገንባት ነው፤
- ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸውን ጥናትና ምርምር በማካሄድ የክልሉን መንግስት ማማከር፡፡
ተልዕኮ
ለህዝብና ለግል ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እና ሌሎች የሲቪክ ማህበራት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ፣ ለችግሮች መፍትሄ የሚሰጥና ጥራት ያለው ስልጠና፣ የማማከር እንዲሁም የምርምርና የማህበረሰብ ልማት አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ወጪ፣ በተገቢውጥራትና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በአመራርና አስተዳደር ልማት መስኮች እንዲሰጡ ለማስቻል ነው።
ራዕይ
የአመራር አካዳሚው በ2022 ዓ.ም በመንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ተወዳዳሪና ከፍተኛ ብቃት ያላቸው መሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን የሚያፈራ የአቅም ግንባታ ማዕከል ሆኖ ማየት ነው።
ዕሴቶች
አካዳሚው የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት እንዲቻለዉ፡-
- ደንበኛ ተኮር እና የላቀ አገልግሎት እንጣለን፣
- ልህቀት በጥረት መርህ እንመራለን፣
- አካዳሚያዊ ነፃነትን እናከብራለን፣
- ለጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን፣
- አሳታፊና ቅንጅታዊ አመራር እንተገብራለን፣
- ሁልጊዜ መማር ፍልስፍናችን ነው፣
- ብዝሀነታችን ጥንካሬያችን ነው፡፡