Skip to main content

የጥናትና ምርምር ዘርፍ

የጥናትና ምርምር ዘርፍ 

አካዲሚው በክልሉ ባሉት የመንግሥትና የግል ሴክተሮች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሲቪክ ማህበራት ዘንድ እየጨመረ የመጣውን ተወዳዳሪ፤ ዕውቀትና ክህሎት እንዲሁም የተሻለ አመለካከት ያለውን የሰው ሃይል ፍላጎት ለማሟላት በአካዲሚው የትምህርትና ስልጠና እና የጥናትና ምርምር የሚሉ ዘርፎች ተዋቅሮዋል፡፡

 

በመሆኑም የጥናትና ምርምር ዘርፍ በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር ሳይንሳዊ የለውጥ ሀሳቦችን በማመንጨት በክልሉ ብሎም በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ይሰራል፡፡