የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ከክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ እና ከፓሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር "የቱሪዝም ና የዕደ ጥብባት ኢንዱስትሪዎች ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚኖራቸው እምቅ አቅም" በሚል ርዕስ ጥናት ለማካሄድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ የግብ ስምምነት ተፈራረሙ።
drupal
Fri, 09/05/2025 - 11:04
ህዳር 2/2017
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ከክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ እና ከፓሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር "የቱሪዝም ና የዕደ ጥብባት ኢንዱስትሪዎች ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚኖራቸው እምቅ አቅም" በሚል ርዕስ ጥናት ለማካሄድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ የግብ ስምምነት ተፈራረሙ።
የፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው በክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በማልማት እና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግና የዕደ ጥብብ ምርቶችን ለስራ ዕድል ፈጠራ የጥናት ስራው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።በሶስቱ ተቋማት መካከል የተካሄደውን ስምምነት ፊርማ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣የአመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንዲሁም የፓሊሲ ጥናትና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አክመል አህመድ በጋራ ማድረግ ችለዋል።
Image