Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ የአመራር እና ፈፃሚዎችን አቅም ግንባታ ስልጠና እና በወሳኝ አጀንዳዎች ያከናወናቸው ጥናቶች ስኬታማ እንደሆኑ ተገለፀ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን አመራር አካዳሚ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።

ሐምሌ 7/2016

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ የአመራር እና ፈፃሚዎችን አቅም ግንባታ ስልጠና እና በወሳኝ አጀንዳዎች ያከናወናቸው ጥናቶች ስኬታማ እንደሆኑ ተገለፀ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን አመራር አካዳሚ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ እና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት በተገኙበት የክልሉን አመራር አካዳሚ የእቅድ ክንውን ግምገማ አከናውኗል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ለቋሚ ኮሚቴው ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል።ቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ተቋሙ የመንግስት ፖሊሲ የማስፈፀም የመፈፀም አቅም ለመገንባት ለአመራሩ እና ፈፃሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠቱ ፤ በክልሉ ቀዳም አጀንዳ በሆነው በዘላቅና አወንታዊ ሠላም ግንባታ ላይ እና ሰው ሀይል የጥናትና ምርምር ሥራዎች ማከናወኑን በጥንካሬ አንስተዋል ።

ተቋሙን በሰው ሀይል እና በሎጂስቲክስ ለማብቃት እየተደረገ ያለውን ጥረትም ቋሚ ኮሚቴው ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት አሳስቧል።የውስጥ ኦዲት አሰራርን ከማጠናከርና ሰው ሀይል ከሟማለት አንጻር በቀጣይ በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑ ቋሚ ኮሚቴው በግምገማው አመላክቷል።

Image
photo