የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ለተቋሙ አመራሮችና ሠረተኞች በሥነ ምግባር መርሆችና እሴቶች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
drupal
Fri, 09/05/2025 - 11:16
ሳጃ ሰኔ 13/2016 ዓ/ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ለተቋሙ አመራሮችና ሠረተኞች በሥነ ምግባር መርሆችና እሴቶች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ ስልጠናዉን ሲያስጀምሩ እንደተነገሩት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ያዘጋጀዉ ስልጠና የተቋሙ አመራሮችና ሠረተኞች የሥነ ምግባር መርሆዎችንና እሴቶችን ተረድተዉ ፤መልካም ሥነ- ምግባር ተላብሰዉ፤ በአገልጋይነት መንፈስ፤ ብልሹ አሠራሮችን በቁርጠኝነት እንዲታገሉ እንዲሁም ተልዕኳቸዉን በታታሪነትና በትጋት እንዲፈፅሙ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራዋል›› ብለዋል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ ሥና ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል አስተባባሪ አቶ ጌታቸዉ አድገህ በስነ ምግባር ምንነት፤መርሆና እሴቶች ላይ መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን አቶ ሳሙኤል ኤሊያስ ደግሞ የመንግስት ሠረተኞች የስነ ምግባር ኮድ ላይ ሰነድ አቅርባዉ ዉይይት ተደርጎ ስልጠናውተጠናቋል፡፡
Image