Skip to main content

የሀገር ኢኮኖሚ ሽግግር ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረገው በቀበሌ ደረጃ በመሆኑ የመዋቅሩን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለፁ።

የሀገር ኢኮኖሚ ሽግግር ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረገው በቀበሌ ደረጃ በመሆኑ የመዋቅሩን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለፁ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለገጠር ቀበሌ ስራ አስኪያጆች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

(ሆሳዕና፣ ታህሳስ 11/2017)፣ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ፣ በአገልጋይ መሪነት፣ በተቀናጀ እቅድ፣ መረጃ አያያዝና አጠቃቀም ላይ በማተኮር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የሀገር ኢኮኖሚ ሽግግር ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረገው በቀበሌ ደረጃ በመሆኑ የመዋቅሩን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ቀበሌ የብልፅግና ምሰሶ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቀበሌ ደረጃ የሚመጣው ለውጥ የሀገርን ለውጥ የሚያመጣ ስለመሆኑም ተናግረዋል።የክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ መንግስት በቀበሌ አደረጃጀት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።የክልሉ ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

ህብረተሰቡን በፍትሃዊነት በማገልገል የተገልጋይ እርካታን ማምጣት፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት ይገባልም ብለዋል አቶ አንተነህ።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሁሉንም ዜጋ ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም የቀበሌ ስራ አስኪያጆች ሚና ጉልህ መሆኑን ተናገረዋል።

የስልጠናውን ግብ ማሳካት መቻሉን የተናገሩት አቶ ተስፋዬ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ስለመስጠቱም ጠቁመዋል።ስራ አስኪጆቹ በስልጠናው መሰረት በየቀበሌያቸው ስልጠናውን ተግባራዊ ስለማድረጋቸው በቀጣይ ክትትል በማድረግ ውጤታማነቱ የሚለካ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ በበኩላቸው የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የተሰጠው ስልጠና ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።የክልሉ መንግሥት ለስልጠናው ትልቅ ትኩረት መስጠቱን አስታውሰው በስልጠናው የተሳተፉ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች በስልጠናው ያገኙትን ተግባራዊ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው መርሃ ግብር የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለስልጠናው ስኬት ላበረከተው አስተዋፅኦ የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

Image
photo