Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከከልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ሴቶች ክንፍ ጋር በመተባበር ከሁሉም የክልሉ መዋቅሮች ለተውጣጡ ሴት አመራሮችና ፈፃሚዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሳጃ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ በሥርዓተ ፆታ አካቶ እና ሴቶች ማብቃት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

(ሳጃ፣ የካቲት 19/2017)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከከልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ሴቶች ክንፍ ጋር በመተባበር ከሁሉም የክልሉ መዋቅሮች ለተውጣጡ ሴት አመራሮችና ፈፃሚዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሳጃ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው በመሠረታዊ የመሪነት ጥበብ ሴቶችን ማብቃት፣ በሥረዓተ ፆታ አካቶ እንዲሁም በሥርዓተ ፆታ አካቶ መመሪያ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።የአመራር አካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ሴቶች የቤትና የሀገር መሠረት ናቸው።ሴቶችና ህፃናትን በመንከባከብ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚኖራቸው ሚና የጎላ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።ያለ ሴቶች ተሳትፎ ሁለንተናዊ እድገትን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት አቶ ተስፋዬ የሴቶች ተሳትፎ ይበልጥ እንዲጎለብት ሴቶችን በስልጠና ማብቃት አስፈላጊ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሐመድናስር የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተተኪ የሴት አመራሮችን ለማፍራትና የሴቶችን ተሳታፊነት ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።

ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በስራ መስካቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉም ኃላፊዋ አሳስበዋል።ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተጠቁሟል።

Image
photo