በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ሴቶችን የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ለሀገር ብልፅግና መረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው አሉ።
በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ሴቶችን የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ለሀገር ብልፅግና መረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው አሉ።
የተከበሩ አቶ አቡቶ አኒቶ፡
የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ጋር በቅንጅት የተዘጋጀ አቅም ግንባታ ስልጠና በሣጃ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው በክብር እንግድነት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ እንዳሉት፤ ሴቶችን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የታቀዱ ስራዎች ውጤት ማምጣት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት ጊዚያት በተለያዩ የስራ መስኮች ተሳትፈው ውጤት ያመጡ ሴቶች ለክልሉ መንግስት እና ለሀገር ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ ችለዋልም ብለዋል።
በክልሉ አመራር አካዳሚ የተጀመረው ሴቶችን የማብቃት እና በክህሎት የመደገፍ ስራ ሴቶችን ውጤታማ እያደረገ እንደሆና ተገልጿል።
የክልሉ አመራር አካዳሚ ዋና ዲሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው አካዳሚው ላለፉት ዓመታት የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ዛሬ የተጀመረው ስልጠና ሴቶችን በማብቃት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።
ለሀገር ሰላም፣ ለህገ-መንግስታዊ ስርዓት መከበርና በማህበራዊ ዘርፍ ልማት ተጠቃሚ መሆን እንዲቻል የሴቶች ተሳትፎ ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
"ሴቶችን ማሰልጠን ሀገርንና ማህበረሰብን እንደማሰልጠን ነው" ሲሉም አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል ስለሆነም በመንግስት መዋቅር ላይ ያሉ ሴቶችን ማሰልጠን በዕውቀትና በክህሎት የታነጹ አመራርና ባለሙያ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።
ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በዋናነትም የመሪነት ክህሎት እና ውጤታማ ተግባቦት እንዲሁም የስርአት ፆታ ማካተትና ሴቶች የማብቃት ስትራቴጂ ላይ ያተኩራል ነው የተባለው ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉደይ ቢሮ ምክትል እና የሴቶች ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም የቢሮ ሀላፊ ተወካይ ወ/ሮ ነጀሚያ ራመቶ
በየመዋቅሩ የሚገኙ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡