ስልጠናው የሴቶችን የመሪነት እውቀት ፣ብቃት፣ ክህሎት፣ ተሳትፏቸውንና ተግባቦታቸውን የሚያጎለብት ነው።
ስልጠናው የሴቶችን የመሪነት እውቀት ፣ብቃት፣ ክህሎት፣ ተሳትፏቸውንና ተግባቦታቸውን የሚያጎለብት ነው። አቶ አብቲ እንሰቦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ የስልጠና ፕሮግራም ም/ዋና ዳይሬክተር።
ሳጃ:- የካቲት 5/2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ በክልሉ በየደረጃው ለሚገኙ የሴት አመራሮችና ባለሙያዎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል በሳጃ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ የስልጠና ፕሮግራሞች ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብቲ እንሰቦ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ስልጠናው የሴቶችን የመሪነት እውቀት፣ክህሎት፣ተሳትፏቸውንና ተግባቦታቸውን እንድያጎለብቱ ታሳብ ተደርጎ እየተሰጠ ነው ብልዋል።
የክልሉ አመራር አካዳሚ መሰል ስልጠናዎችን በየጊዜው ለሚመለከታቸው አካላት እየሰጠ የክልሉን የማስፈጸምና የመፈጸም አቅም እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አክለውም ይኼኛው ስልጠና ከየካቲት 4_6/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅና ዓላማውንም እያሳካ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
በስልጠና መድረኩ ላይ ተሳታፊ አንዳንድ ሴት አመራሮችና ባለሙያዎች እንደገለጹት የክልሉ አመራር አካዳሚ ሴቶች የአመራርነት ሚናን በብቃትና በተግባቦት እንድወጡ፣ አቀናጅቶ እንዲመሩ፣የማህበረሰብ አገልጋይነትን ጥበብ እንድላበሱ እና ተልዕኮዎቻቸውን በብቃት እንዲወጡ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን በመግለጽ አመራር አካዳሚውን አመስግነዋል።
አያይዘውም አመራር አካዳሚው በቀጣይም መሰል ስልጠናዎችን እስከታችኛው እርከን ድረስ አስፍቶ የአቅም ግንባታ ስራውን እንዲሰራ አስተያየታቸውን ገልጿል።
በስልጠና መድረኩ የአመራር አካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱን ጨምሮ የአካዳሚው ም/ዳይሬክተሮች፣የዞንና ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የሴቶች ማህበር፣ ክንፍ ኃላፊዎች፣ በክልል ቢሮ ያሉ የስርዓተ ጾታ ተወካዮች፣ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።