ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል!!!


- የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
(ሳጃ፣ ሐምሌ 10/2018)፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአመራር አካዳሚን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።
የአመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ የዕቅድ ክንውን ሪፖርታቸውን ለቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ ከሪፖርቱ መነሻ ቋሚ ኮሚቴው የቃል ግብረ መልስ ሰጥቷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ፣ በበጀት አመቱ በተቋሙ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን መገምገሙን ጠቅሰው፣ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
አካዳሚው በስልጠና እና በጥናትና ምርምር ትልልቅና ሞዴል የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት የክልሉን አስፈፃሚ ተቋማት የመፈጸምና የማስፈፀም አቅም እንዲያሳድጉ የበኩሉን ሚና በመወጣቱ ቋሚ ኮሚቴ አመስግነዋል ።
ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ፣ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አንስተዋል።
በዚህ መሠረት ተቋሙ ለበለጠ ውጤታማነት የስልጠና ፕሮግራሞችን በማስፋት በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ አመራርሮችና ፈፃሚዎችን በብዛት እና በጥራት በማሰልጠን የባለድርሻ አካለት ተሳትፎን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ተግባራዊ ማድረግና የተሰሩ ጥናቶች ውጤት በፖሊሲ ቀረጻ እና በተግባር ላይ እንዲውሉ በማድረግ ተጽእኖዋቸውን መከታተል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የላይብሬሪ አገልግሎት ዲጂታለይዝ ማድረግ እና ድህረ-ገፅ አጠቃቀም ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።