የኮሚሽኑን አመራሮች አቅም በመገንባት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት ይሠራል!!
የኮሚሽኑን አመራሮች አቅም በመገንባት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት ይሠራል!!
ሳጃ፣ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ከክልሉ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽኑን አመራሮች አቅም ለመገንባት የሚያስችል የጋራ የግብ ስምምነት በሆሳዕና ከተማ ተፈራርመዋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሽ ሁሴን፣ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽኑን አመራሮች አቅም በመገንባት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅማቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናውም ከክልል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በፓርቲው የአሠራር ሥርዓቶች፣ መመሪያዎች፣ ደንቦችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
የክልሉ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው፣ አካዳሚው በፓርቲው የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ ለማላቅ ዘመኑን የዋጀና ውጤታማ ልያደርግ የሚችል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን አብራርተዋል።
አካዳሚው በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት በመወጣት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ከመስጠት ባለፈ የጥናትና ምርምር ሥራዎችንም እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው የፓርቲውን የአፈጻጸም ጥራት በማሳደግ ጠንካራና ብቁ ፓርቲ ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

